የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ
መጠን
በአለፈው ጥናቶቻችን በተለያዩ ምልከታዎች ላይ በግላችን እንድንሠራቸው የተሰጡ ነበሩ፡፡ አንዳንዶቹ ቀለል ያሉ ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ጠንከርና ጊዜ የሚጠይቁ ሆነው እንዳገኛችኋቸው አስባለሁ፡፡ የዛሬዎቹ ምልከታዎች ግን በጣም ቀላል ሳይሆኑ አይቀሩም ብዬ እገምታለሁ፡፡ ቀላል ስለሆኑ ሁላችሁም ሞክራችኋል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በመጀመሪያ ሮሜ ምዕራፍ 6ን በሙሉ ምልከታ አድርገን ጥያቄና መልስ የሆኑትን እንድናወጣ ተሰጥቶ ነበር፡፡ Read more…