የሰዋስው ችግር

የዛሬውን ትምህርት ስለ ሰዋስው ችግር ከማየታችን በፊት፣ ባለፈው ለተጠየቁት ጥያቄዎች የሰጣችሁትን መልስ፣ ዛሬ አብረን በአንድ ክፍል ውስጥ ባንሆንም በአጠገባችሁ ቆሜ እንዳለሁና እንደ ማስተምር አድርጋችሁ ተከታተሉ፡፡  በመጀመሪያ የተሰጡት የቃላት ጥናት በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 17፡17-22 ላይ የሚገኙት ሲሆኑ፣ ኤፊቆሮስና ኢስጦኢኮች የተባሉት በሦስተኛው ምዕተ ዓመት ላይ የተነሡ የግሪክ ፈላስፎች ሲሆኑ፣ ተከታዮቻቸውም በእነዚህ ስሞች Read more…

ጥያቄ

በባለፈው ጥናቶቻችን በተወሰኑ ክፍሎች ላይ በየጊዜው ምልከታዎች እንድታደርጉ መሰጠታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ምን ያህል እንደ ጠቀማችሁ ባላውቅም፣ በትምህርቶቹ ጠቃሚ ነገር ካገኛችሁ፣ በየጊዜው ሠርታችሁ እንደምትጠብቁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ አለበለዚያ ከዚህ የሚሰጠውን ብቻ የምትጠብቁ ከሆነ፣ ብዙ ተጠቃሚዎች ላትሆኑ ትችላላችሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ በመጀመሪያ በዘዳግም ምዕራፍ 28 ላይ ትእዛዝና ማስጠንቀቂያ የሆኑትን እንድትመለከቱ በተሰጠው መሠረት ምን  አገኛችሁ? Read more…