ተሸነፈ

ታላቁ ጠላት የንባብ ክፍል፡- ዮሐንስ 11፡1-27 ‹‹ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፣ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል›› ቁ. 25 የአልዓዛር እህቶች ማርታና ማርያም ወንድማቸው በታመመ ጊዜ፣ ኢየሱስ መጥቶ እንዲፈውስላቸው  መልእክተኛ ወደ እርሱ ላኩ፡፡ ይሁንና ኢየሱስ አልዓዛር ከመሞቱ በፊት ሊደርስላቸው የወደደ አይመስልም፡፡ አንዳንዴ እግዚአብሔር የተመኘነውን ነገር በፈለግነው ጊዜ አያደርግልንም፡፡ እንዲያውም በአልዓዛር ሞት ደስ Read more…

ሁሉን ያስችላል

‹‹እርሱን … እንዳውቅ››                                   የንባብ ክፍል፡- ፊልጵስዩስ 3  ‹‹እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳወቅ በመከራውም እንድካፈል … እመኛለሁ›› ቁ. 10-11 ሐዋርያው ቀደም ሲልም፡- ክርስቶስን በማወቅ ስለሚገኘው የከበረ እውቀት ይናገራል፡፡ ክርስቶስን ማወቅ ከንቱ ውዳሴ የሆነ የአእምሮ እውቀት፣ ቃሉን መጠቃቀስና የታሪክ እውቀት አይደለም፡፡ ስለ አንዳንድ ሰው የምናውቀው ሐቅ፣ ኑሮና ልማድ፣ የመሳሰለ እውቀት አይደለም፡፡ የአንድን ሰው Read more…

የዓለም ብርሃን

‹‹የዓለም ብርሃን››  የንባብ ክፍል፡- ዮሐንስ 8፡12-20    ‹‹እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን   ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም›› ቁ. 12 ብርሃን አስገራሚ ነገር ነው፤ እስቲ አስቡት ያለ ብርሃን መኖር ይቻላልን? ፀሐይ ከቶ ባትወጣ ጨረቃና ከዋክብት ብርሃናቸውን ቢከለክሉ ይህች ዓለም እንዴት አስከፊ በሆነች? ከሰይጣን ተጽዕኖ የተነሣ ዓለማችን በመንፈሳዊ ሁኔታ በጨለማ የተያዘችና Read more…

መከራው

የክርስቶስ መከራውና ክብሩ ‹‹ጌታችን ኢየሱስ የደረሰበት መከራ እጅግ ከፍተኛ ሲሆን፣ ይህም መሞቱ፣ መቀበሩና ወደ ሲዖልም መውረዱ ነበረ፤ እነዚህን ሁናቴዎች የታገሠውም ሰዎችን ከኀጢአታቸው ለማዳን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ እየተከበረ ሲሄድ ግን በትንሣኤና በዕርገት ሁኔታዎች ዐልፎ በአብ ቀኝ ተቀመጠ፤ እዚያም የዳግም ምጽአቱን ጊዜ ይጠብቃል›› (ትምህርተ ክርስቶስ በቄስ ማንሰል ገጽ 198) ሲሉ መከራውና ክብሩን Read more…

የመላእክት አገልግሎት

የመላእክት ሥራቸው፡- ስለ መላእክት ማንነታቸውንና ስሞቻቸውን ከዚህ ቀደም ብለን የተመለከትን  ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በክርስቶስና በአማኞች ሕይወት የሰጡትን አገልግሎትና ሥራ እናጠናለን፡፡ መላእክት የማይታዩ ከሆነ ሥራቸውን ማን ሊመለከት ይችላል ተብሎ የሚጠየቅ ጥያቄ ሊኖር ይችላል? እኛ ሥራቸውን አየን አላየን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሥራ እንዳላቸው ከነገረን መቀበል አለብን፡፡ ስለዚህ መላእክት እግዚአብሔርን ከማገልገል ውጭ የተለያዩ ሥራዎች Read more…

የቃሉ አስፈላጊነት (ክፍል 1)

የመጽሐፍ ቅዱስ አስፈላጊነት  6.1 የቃሉ አንድነት ባለፈው ጥናታችን መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ተመለክተን ነበር፤ እውነተኛ የአምላክ ቃል ከሆነ፤ ለእኛ አስፈላጊያችን መሆኑን በዚህ ጥናታችን እንመለከታለን፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን አስፈላጊነት በስፋት ከማየታችን በፊት፣ አስቀድመን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አንድነት እንመልከት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይና አዲስ ኪዳን ተብሎ በሁለት ክፍል መከፈሉንም ቀደም ብለን ተመልክተናል፡፡ Read more…

ቀኖና (ክፍል 2)

 4.2 የአዲስ ኪዳን  በአዲስ ኪዳን ያሉትን 27 መጻሕፍት ቤተ ክርስቲያን ቀኖና (መለኪያ) አዘጋጅታ የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት ለመቀበል የተጠቀመችበትንና የሄደችበትን የሂደት መለኪያዎች እንመልከት፡፡ አንድ መጽሐፍ በቀኖና ውስጥ ገብቶ የሚቆጠረው ደራሲው እግዚአብሔር ራሱ ሆኖ ሰው ጽፎት ሲገኝ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የቀኖና መጻሕፍትን ከአዋልድ መጻሕፍት እንዴት እንደለዩና ቀኖና መቼ እንደ ተወሰነ በመቀጠል እንመለከታለን፡፡ Read more…

የትምህርተ-መለኮት ችግር

የዛሬውን ትምህርት ስለ ትምህርተ-መለኮት ችግር ከማየታችን በፊት፣ ባለፈው ለተጠየቁት ጥያቄዎች የሰጣችሁትን መልስ፣ ዛሬ አብረን እያስተያየን ራሳችሁን እያረማችሁና ማርክ እየሰጣችሁ ተከታተሉ፡፡  በመጀመሪያ ለጥናታችን የተሰጠን ክፍል ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 4፡4 ላይ የሚገኘው ‹‹በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት›› የሚለው ነበር፡፡ በእነዚህ አራት ቃላት የተገለጸውን ታሪክ ለመተንተን ብዙ ሰዓት ይወስዳል፡፡ የታሪኩን ጅማሬ የምናገኘው በብሉይ ኪዳን Read more…