ትንቢት

የዛሬውን ትምህርት ስለ ትንቢት ከማየታችን በፊት በባለፈው በጥበብ መጻሕፍት (ግጥም፣ ቅኔ) ዙሪያ ለተጠየቁት ጥያቄዎች የተሰጡትን መልሶች በአካል ክፍል ውስጥ እንደሆንን በማሰብ አብረን እንመልከት፡፡  የመጀመሪያው የተሰጠው መዝሙር 5፡1 ላይ ሲሆን፣ መልሱም ከተሰጡት ምርጫዎች፣ ሀ.ተመሳሳይ ተጓዳኝ የሚለው መልሳችሁ ከሆነ፣ መልሳችሁ ትክክል ነው፡፡ ‹‹አቤቱ ቃሌን አድምጥ፣ ጩኸቴንም አስተውል››፣ የሚለውን ግጥም ተመሳሳይ ተጓዳኝ የሚያደርገው፣ Read more…

ሥነ-ጽሑፍ

የዕለቱን ትምህርት ከማየታችን በፊት፣ በየጊዜው እንደምናደርገው አስቀድማችሁ እንድትሠሩት በተሰጣችሁ ክፍል ላይ ትኩረት በማድረግ ጥናታችንን እንቀጥላለን፡፡ የመጀመሪያው በኢሳይያስ 7፡13 ላይ ተመልከቱ ተብሎ በተሰጣችሁ ላይ ‹‹እርሱም አለ፡-እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፡-  ስሙ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? ‹‹እርሱም›› የሚለው ተውላጠ ስም ተክቶ የገባው ‹ኢሳይያስ› የሚለውን ስም ነው፡፡(በመደበኛው ትርጉም ሲተረጉሙ ‹ኢሳይያስ› ብለው ስለሆነ፣ ያለ Read more…

የተሻለ ቃል ኪዳን

በቀደሙት የዕብራውያን ጥናቶቻችን ጸሐፊው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በማተኮር ከነብያትና ከመላእክት፣ ከሙሴ፣ ከኢያሱና ከአሮን አገልግሎት ሁሉ አገልግሎቱ እንደሚበልጥ አሳይቶናል፡፡ አሁን ደግሞ በመቀጠል እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል የገባልን ቃል ኪዳን የላቀ መሆኑን ያሳየናል፡፡ በፊተኛው ቃል ኪዳን ሰዎች በሁለት መንገዶች ተካፋዮች ነበሩ፡፡  እያንዳንዱ የአይሁድ ቤተሰብ በግዝረት የቃል ኪዳን ተሳታፊ ነበር፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የቃል ኪዳን Read more…

አለመታዘዝ

‹‹በአንድ ድንጊያ ሁለት ወፍ››  እንደሚሉት፣ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ሁለት ሦስት ሐሳቦችን በአንድ ጊዜ መግለጽ ይችላል፡፡ ስለዚህ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሁለትን ስንመለከት የሁለት ነገሮች ፍጻሜ ነው፡፡ የመጀመሪያው ለወንጌሉ ሥራ ኃይል የሚሆን የተስፋ ፍጻሜ ሲሆን፣ ሁለተኛው ወንጌልን ባለመቀበላቸውና ባለመታዘዛቸው የሚመጣ የፍርድ ፍጻሜን ያመለክታል፡፡ በብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስና መንፈስ ቅዱስ የተነገሩ ትንቢቶች ለአይሁዶች Read more…