መልካም ልደት

ውድ የተልዕኮ ኦን ላይን (online) አገልግሎት ተከታታዮች ላለፉት አራት ዓመታት ተልዕኮ teleko.org በሚለው ድህረ ገጽ እና የሶሻል ሚዲያ ቴሌግራምና ፌስ ቡክ ተከታታይ የሆኑ ጽሑፎችንና ትምህርቶችን ስናጋራ ቆይተናል፡፡ በዚህ በልደት ሰሞን  ‹‹መልካም ልደት›› በሚል የተዘጋጀ ጽሑፍ ተልዕኮ teleko.org በሚለው ድህረ ገጽ እናጋራችኋለን፡፡ አሁን በዚህ ሳምንት ልደትን ልናከብር እየተዘጋጀን ባለንበት ጊዜ ከቅዱስ Read more…

መጠራት

 ለ) የወልድ ምርጫ፡- ስለ አብ ባደረግነው ጥናት፤ በድነት ሥራ ውስጥ እግዚአብሔር አብ ልጁን በሚልክበት ጊዜ ማን እንደሚያምንና እንደማያምን በመለኮታዊ ዕውቀቱ አስቀድሞ ማወቅ፤ መወሰን፤ መጥራት፤ ማጽደቅና ማክበር እንደሚከናወኑ ተመልክተናል፡፡ አብ ልጁን ሲልክ ልጁም ኢየሱስ ክርስቶስ ተልዕኮውን ተቀብሎ ተግባራዊ ሲያደርግ በቃሉ ውስጥ እናያለን፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ እንዲህ ይላል ‹‹እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ በዚህ Read more…

አጋንንት

2.2 አጋንንት፡-ስለ አጋንንት ከማጥናታችን በፊት ያጠናነው ስለ ሰይጣን ነበር፤ እርሱም አለቃቸው ሲሆን፤ አጋንንት ደግሞ ተከታዮቹ ናቸው፡፡ ይህን ሐሳብ በማቴዎስ 12፡24 ላይ ስንመለከት ‹‹ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም›› ከሚለው አባባላቸው ማየት የምንችለው አለቃና ጭፍራ እንዳላቸው ነው፡፡ በዚህ መሠረት አጋንንት የአለቃቸውን የሰይጣንን ዕቅድ ተላላኪዎችና ፈጻሚዎችናቸው፡፡ አጋንንት ሁለት ዓይነት Read more…

የእግዚአብሔር ባሕርያት (ክፍል 4)

3.10 ሁሉን አዋቂ ነው፡- ባለፈው ጥናታችን እግዚአብሔር ዘላለማዊ፣ ፍቅርና ነፃ መሆኑን ተመልክተን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ፣ ሁሉን ቻይና ከሁሉ በላይ መሆኑን በጥናታችን እንመለከታለን፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው፣ ስንል ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን፣ ዛሬም ያለውን፣ ወደ ፊትም የሚመጣውን ሁሉ ያውቃል፡፡ ዛሬ ብዙ ሳይንቲስቶችና ጠበብት ባሉበት አገር ዓለም በኮቢድ 19 Read more…

ምልከታ

የተለያዩ ምልከታዎች ማድረግ  በሰባት መጠየቂያ ቃላት ከመጠቀም ቀጥሎ የምንመለከተው የተለያዩ ምልከታዎች ስለ ማድረግ ይሆናል፡፡ በዚህ መንገድ እየጠየቅን ስናጠና የነበረውን ማንኛውንም ክፍል፣ እንደገና የተለያዩ ምልከታዎች በማድረግ ማጥናት ያስፈልገናል፡፡ የአንድ ሰው በሽታ የሚታወቀው ልዩ ልዩ ምርመራ በማድረግ ነው፡፡ የተለያዩ በሽታዎች በተለያየ ምርመራ ይገኛሉ፡፡ በሽንት፣ በደም፣ በኤስሬ፣ በአልትራ ሳውንድና በሲቲ ስካን በመሳሰሉት ምርመራዎች Read more…

ፈቃዱን ማወቅ

የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት እናውቃለን? በእግዚአብሔር ፈቃድ ዙሪያ ስንት መጽሐፍ አንብበናል? ምን ያህል ጊዜ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተነጋግረናል? የሚያረካ መልስ አግኝተን ይሆን? በግላችን፣ በቤተ ሰባችንና በአገራችን እየሆኑ ያሉት ነገሮች በማን ፈቃድ የሚሆኑ ናቸው?  መራብና መጠማት፣  መደኽየትና መበልጸግ፣ መከራና ሞት፣  ራስን ሰቅሎ መሞት፣ በመኪና አደጋ መሞት፣ በዘራፊ መገደል፣ ለመሳሰሉት ሁሉ ተጠያቂው ማነው? Read more…