የቃሉ አስፈላጊነት (ክፍል 1)

የመጽሐፍ ቅዱስ አስፈላጊነት  6.1 የቃሉ አንድነት ባለፈው ጥናታችን መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ተመለክተን ነበር፤ እውነተኛ የአምላክ ቃል ከሆነ፤ ለእኛ አስፈላጊያችን መሆኑን በዚህ ጥናታችን እንመለከታለን፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን አስፈላጊነት በስፋት ከማየታችን በፊት፣ አስቀድመን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አንድነት እንመልከት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይና አዲስ ኪዳን ተብሎ በሁለት ክፍል መከፈሉንም ቀደም ብለን ተመልክተናል፡፡ Read more…

እውነተኛ ቃል

1.5 እውነተኛ ቃል የእግዚአብሔር ቃል ከሰዎች ቃል ሁሉ የበለጠና የላቀ እውነተኛና ታማኝ ቃል ነው፡፡ እግዚአብሔር በየዘመናቱ  ለሰዎች የተናገረውን ሲፈጽም የኖረ፤ አሁንም እየፈጸመ የሚገኝ፤ ወደ ፊትም እየፈጸመ የሚኖር አምላክ ነው፡፡ እኛ ፍጥረቶቹ የሆንን ሰዎች እንኳን በምንነጋገራቸው እውነተኛና ታማኝ ቃሎች አማካይነት እርስ በርሳችን በመተማመን መልእክት እንለዋወጣለን፣ ሀሳብ ለሀሳብ እንግባባለን፤ ገንዘብ እንኳን ሳይቀር Read more…

ቀኖና (ክፍል 2)

 4.2 የአዲስ ኪዳን  በአዲስ ኪዳን ያሉትን 27 መጻሕፍት ቤተ ክርስቲያን ቀኖና (መለኪያ) አዘጋጅታ የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት ለመቀበል የተጠቀመችበትንና የሄደችበትን የሂደት መለኪያዎች እንመልከት፡፡ አንድ መጽሐፍ በቀኖና ውስጥ ገብቶ የሚቆጠረው ደራሲው እግዚአብሔር ራሱ ሆኖ ሰው ጽፎት ሲገኝ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የቀኖና መጻሕፍትን ከአዋልድ መጻሕፍት እንዴት እንደለዩና ቀኖና መቼ እንደ ተወሰነ በመቀጠል እንመለከታለን፡፡ Read more…

ቀኖና (ክፍል 1)

1.4 ቀኖና (Canon)   4.1 የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ በቀኖና (ካኖን) ያለፈ መጽሐፍ ሲሆን፣ ቄስ ኮሊን ማንሰል ‹‹ቀኖና (Canon) ከግሪክ የተገኘ ቃል ሆኖ ሕግ፣ መለኪያ፣ መገምገሚያ ማለት ነው›› እንግሊዝኛውም ቃል የመጣው ከግሪክ ነው ይላሉ፡፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ቀኖና ማለት ለክርስትና እምነት መመሪያ የሚሆኑትን እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ያለባቸውን መጻሕፍት መሰብሰብና መምረጥ ማለት ነው፡፡ (2ጢሞ.3፡16-17) Read more…

የተገለጠ ቃል

1. 3 የቃሉ መገለጥ  3.1መገለጥ ምንድን ነው ?   መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር መገለጥ ቢሆንም፣ ወንድም ምኒልክ እንዲህ ይላሉ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ቋንቋ የተጻፈ የእግዚአብሔር ሥልጣናዊ ቃል ነው›› ትርጉሙንም እንዲህ አስቀምጠውታል ‹‹መገለጥ መከሰት፣ መታወቅ፣ መታየት፣ በዚሁም መገኘት ማለት ነው›› (መጽሐፍ ቅዱስና የትርጓሜ ስልቱ ምኒልክ አስፋው ገጽ 51፣ 53) እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆች Read more…

ቃል ኪዳን

2 ቃል ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ የቃል ኪዳን መጽሐፍ ነው፤ ቃል ኪዳኑም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የተደረገ ሲሆን፣ ከግለሰቦችና ከሕዝቦች ጋር ያደረገው ስምምነት እንደ ሆነ ከተጻፈው ቃሉ ማግኘትና መረዳት እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የመጣውና የተገለጠው በየጊዜው በሚያድግ መገለጥ (Progressive Revelation) እንደ ሆነ፣ ከሰዎች ጋር ባደረገው ቃል ኪዳን አማካኝነት ማየትና መረዳት ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር በብሉይ Read more…

መጽሐፍ ቅዱስ

ሀ) አስተምህሮተ እግዚአብሔር     1) አስተምህሮተ መጽሐፍ ቅዱስ መግቢያ፡- በዚህ አስተምህሮተ እግዚአብሔር በሚለው ርዕስ ሥር አስቀድመን የምናጠናው፤ ስለ አስተምህሮተ መጽሐፍ ቅዱስ ይሆናል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ  ስለ እግዚአብሔር  መገለጥ (Revelation) የሚገልጽና የሚያስረዳ መጽሐፍ በመሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በመንፈስ ቅዱስና በሰዎች ሆኖ የተናገረው የራሱ ቃል ስለ ሆነ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ስለ እግዚአብሔር Read more…

መግቢያ / አስተምህሮ

ክርስታናዊ አስተምህሮን ወይም መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮን (ዶክትሪን) ለመጻፍ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች መጽሐፍ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር፣ ክርስቶስ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ ድነት፣ ቤተ ክርስቲያን፣ መላእክት፣ የመጨረሻው ዘመን እያሉ ርዕስ ሰጥተውና ከፋፍለው አልጻፉትም፤ ምክንያቱም ጸሐፊዎቹ በየዘመናቱ ለተነሱ ችግሮች የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ እየሰሙ መፍትሔ ለመስጠት በጽሑፍ የወሰዱትን ርምጃ ነው፣ በቃሉ ተጽፎ የምናገኘው፡፡ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትንና ያልተዘረዘሩት Read more…