ኢየሱስ

አስተምህሮተ ሥጋዌ (ኢየሱስ) ባለፈው ጥናታችን የተመለከትነው ስለ ሰው ጅማሬና ውድቀት እንደ ነበረ የሚታወስ ነው፤ ሰው የተሰጠውን ትእዛዝ አፍርሶ፣ አምላክ ለመሆን የነበረው ምኞት ከስሞ፣ ከኤደን ገነት ተባሮ መኖር መጀመሩን ነበር፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሰውን በሞት ሁኔታ እንዳለ ሊተወው ይችል ነበር፤ ነገር ግን ስለወደደው ሊያድነው ዐቀደ፤ ዕቅዱም አንድያ ልጁን ወደ ዓለም መላክ፤ በዓለምም ተገኝቶ Read more…

ኃጢአት

1፡2  የሰው ውድቀት ሰው በኃጢአት ከመውደቁ በፊት፣ በእግዚአብሔር ሲፈጠር በራሱ ነፃ ፈቃድ፣ ምርጫ ማድረግ የሚችል ተደርጎ የተፈጠረ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው አንድ ቦታ እንደ ድንጋይ ወይም የቤት ዕቃ ተጎልቶ የሚቀመጥ፣ የማይንቀሳቀስ ሳይሆን፣ በራሱ ሐሳብና ዕቅድ መሠረት የሚንቀሳቀስ፣ የሚሠራ፣ የሚበላ፣ የሚጠጣና የሚተኛ … አስደናቂ ፈቃድና ምርጫ ማድረግ እንዲችል የተሰጠው ፍጡር ነበር፡፡ ይህን Read more…

ሰው

ለ) አስተምህሮተ ክርስቶስ አስተምህሮተ ሰው በክፍል አንድ አስተምህሮተ እግዚአብሔር በሚለው ሥር መጽሐፍ ቅዱስ፣ እግዚአብሔርና መላእክት የሚሉትን ሦስት ትምህርቶችን ተመለከትን፡፡ አሁን ደግሞ አስተምህሮተ ክርስቶስ የሚለውን ክፍል ሁለት ትምህርት ጀምረን፤ በሥሩ ያሉትን አስተምህሮተሰው፣ አስተምህሮተሰብዓዊነትና መለኮታዊነት የሚሉትን ሦስት ትምህርቶችን  እናጠናለን፡፡ በፍልስፍናም ሆነ በእምነት የሰውን ማንነት ለማወቅ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲጠየቁ ቆይተዋል፡፡ ጥያቄዎቹም ሰው ማነው? Read more…

አጋንንት

2.2 አጋንንት፡-ስለ አጋንንት ከማጥናታችን በፊት ያጠናነው ስለ ሰይጣን ነበር፤ እርሱም አለቃቸው ሲሆን፤ አጋንንት ደግሞ ተከታዮቹ ናቸው፡፡ ይህን ሐሳብ በማቴዎስ 12፡24 ላይ ስንመለከት ‹‹ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም›› ከሚለው አባባላቸው ማየት የምንችለው አለቃና ጭፍራ እንዳላቸው ነው፡፡ በዚህ መሠረት አጋንንት የአለቃቸውን የሰይጣንን ዕቅድ ተላላኪዎችና ፈጻሚዎችናቸው፡፡ አጋንንት ሁለት ዓይነት Read more…

ሰይጣን

3.2 የወደቁ መላእክት 2፡1 ሰይጣን፡- በባለፈው ጥናታችን መላእክት ያልወደቁ የወደቁት ብለን ተመልክተናል፤ አሁን በመቀጠል በወደቁ መላእክት ላይ ትኩረታችንን እናደርጋለን፡፡ መላእክት አስቀድሞ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ የከበሩ መላእክት ነበሩ፡፡ ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው ምክንያት የማገልገላቸውን መብትና ክብር አጡ፡፡ ስለ ወደቁ መላእክት ስንመለከት ያልታሰሩና የታሰሩ መላእክት ብለንበሁለት ከፍለን እንመለከታቸዋለን፡፡ ስለ ውድቀታቸው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሁሉ በተቻለ Read more…

የመላእክት አገልግሎት

የመላእክት ሥራቸው፡- ስለ መላእክት ማንነታቸውንና ስሞቻቸውን ከዚህ ቀደም ብለን የተመለከትን  ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በክርስቶስና በአማኞች ሕይወት የሰጡትን አገልግሎትና ሥራ እናጠናለን፡፡ መላእክት የማይታዩ ከሆነ ሥራቸውን ማን ሊመለከት ይችላል ተብሎ የሚጠየቅ ጥያቄ ሊኖር ይችላል? እኛ ሥራቸውን አየን አላየን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሥራ እንዳላቸው ከነገረን መቀበል አለብን፡፡ ስለዚህ መላእክት እግዚአብሔርን ከማገልገል ውጭ የተለያዩ ሥራዎች Read more…

መላእክት

አስተምህሮተ መላእክት ያልወደቁ መላእክት በቀደመው ጥናታችን የተመለከትነው አስተምህሮተ እግዚአብሔር የሚል ነበር፤ በመቀጠል የምንመለከተው አስተምህሮተ መላእክት የሚለውን ሦስተኛውን ርዕሳችንን ይሆናል፡፡ ስለ መላእክት መፈጠር ስናጠና መቼ እንደ ተፈጠሩ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ምንም ሥፍራ የለውም፡፡ መላእክት እግዚአብሔር  ከፈጠራቸው ፍጥረታት መካከል አንዱ መሆናቸው ቃሉ ስለሚነግረን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ሰዎች  የመላእክትን መኖር ቢያምኑም ባያምኑም  እርግጠኛ Read more…

ሥላሴ (ክፍል 2)

ወልድ፡- ‹‹እግዚአብሔር ወልድ››  ከሥላሴ አካል አንዱ ሲሆን፤  የሰው ልጆችን ለማዳን ወደዚህ ምድር ከድንግል ማርያም ሥጋ ነስቶ በመምጣትና ለኃጢአታችን በመስቀል ላይ በመሞት ከአባቱ ጋር ያስታረቀን ወልድ ነው፡፡  ሐዋርያው ጳውሎስ በቲቶ መልእክቱ ምዕራፍ 1፡1-4 ባለው ክፍል ላይ  ‹‹… የማይዋሽ እግዚአብሔር(አብ) ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ፣ በዘመኑም ጊዜ፣ መድኃኒታችን እግዚአብሔር (ወልድ) እንዳዘዘ፣ ለእኔ Read more…

ሥላሴ (ክፍል 1)

  የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ባለፈው ጥናታችን ያጠናነው የእግዚአብሔርን መጠሪያ ስሞች ሲሆን በመቀጠል የምናጠናው የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት ስለሚገልጠው ሥላሴ ይሆናል፡፡ በቄስ ማንሰል ስለ ሥላሴ እንዲህ ይላሉ ‹‹በአንዱ እግዚዘብሔር ዘንድ ሦስትነት አለ፤ በመካከላቸው ‹‹እኔ … አንተ… እርሱ›› የሚል አጠራር አለ፡፡ እግዚአብሔር የአስተርእዮን (መገለጥን) ተግባር ወደ ፍጻሜ ሲያደርሰው፣ ልጁንና መንፈሱን ወደ ዓለም በመላክ Read more…

የእግዚአብሔር መጠሪያ

2.4 የእግዚአብሔር መጠሪያ ስለ አስተምህሮተ እግዚአብሔር ስንጀምር፣ የእግዚአብሔር መኖር በሚለው ርዕስ ሥር እንደተመለከትነው፣ ቃሉ ከሁለት ጥምር ከሆኑ የግዕዝ ቃሎች የመጣና ትርጉሙም ‹‹የሕዝቦች ጌታ›› ማለት እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ ይህ በአማርኛችን ሲሆን፣ በመቀጠል እግዚአብሔር የሚለውን መጠሪያ ስም በመሠረታዊ ቋንቋው እንመለከተዋለን፡፡ ብሉይ ኪዳን በተጻፈበት በዕብራይስጥ ቋንቋ ስናጠና ስም መለያ፣ መጠሪያና የማንነት መገለጫ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ Read more…