የድነት ውጤት

2.3 የድነት ውጤት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰማ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስለ ኃጢአቱ ይወቀሳል፤ በኃጢአቱም ምክንያት ሞትና ኩነኔ እንዳለበት ሲረዳ፣ በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት አማካኝነት ንስሐ በመግባት ክርስቶስን ሲያምን በመንፈስ ቅዱስ እንደሚታተም ተመልክተናል፡፡ ቃሉም መንፈስ ቅዱስም የኃጢአቱ ዋጋ በክርስቶስ እንደ ተከፈለለት ሲያውጁለት ንስሐ በመግባት ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ልቡ በማስገባት ያምናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ‹‹በእርሱ Read more…

በሐዋርያት ሥራ

የመንፈስ ቅዱስ አሠራር ዳሰሳ፡- ከላይ  እንደ ተመለከትነው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ሙላት ለሐዋርያት ለአገልግሎታቸው አስፈላጊዎች እንደ ነበሩ፤ ለእኛም እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ አሠራር በተለያየ መልክና መንገድ ስለሚገለጥ አዳዲስ አማኞች በመንፈስ ቅዱስ በሚሞሉበት ጊዜ አንዳንድ ያልተለመዱ ነገሮች ሊያሳዩና ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ በአንድ ጊዜ ሲጠመቁና ሲሞሉ የተፈጸሙትን ድርጊቶች ስንመለከት፤ ድንገት Read more…

በአማኝ ሕይወት (ክፍል 2)

ይሞላል፡- ቀደም ባሉት ሁለት ጥናቶቻችን እንዳየነው፤ በነቢያቶችና በጌታ በራሱ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተነገሩት ትንቢቶች በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2፡4 ላይ መፈጸሙን ተመልክተናል፡፡ ትንቢቱ በመፈጸሙ ላይ ብዙ ችግር የለንም፤ ችግራችን ያለው 2፡4 ጥምቀት ነው ወይስ ሙላት ነው የሚለው ላይ ነበር፡፡ ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ ስንሰጥ ሁለቱንም ያመለክታል ብለን መልሰናል፤ በመቀጠል በጥምቀትና በሙላት መካከል Read more…

በአማኝ ሕይወት (ክፍል 1)

በባለፈው ጥናታችን መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን በክርስቶስና በአማኝ ሕይወት የሠራውን እየተመለከትን መቆየታችን የሚታወስ ነው፡፡ ጥናታችንን ያቆምነው መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ሕይወት ስለሚሠረው ሥራ ስንመለከት፤ ስለ ክርስቶስ ምስክርነት እንደሚሰጥ፣ ዳግም ልደት እንደሚሰጥ፣ የእግዚአብሔር ልጅና አዲስ ፍጥረት እንደሚያደርግ ተመልክተን ነበር፡፡ በመቀጠልም በጣም አስቸጋሪና አከራካሪ ወደ ሆነው፤ በመንፈስ ቅዱስ አማኙን እንደሚያጠምቅ፤ በብሉይ Read more…

በክርስቶስ ሕይወት

በአዲስ ኪዳን፡- የመንፈስ ቅዱስን ማንነትና በብሉይ ኪዳን ጊዜ፣ ሥላሴ ባቀዱት ዕቅድ መሠረት የሥራ ድርሻውን ሲወጣ እንደ ነበረ ተመልክተናል፡፡ በብሉይ ኪዳን በድርሻቸው መሠረት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ሲወጡ እንደተመለከትነው፤ በአዲስ ኪዳንም ደግሞ እያንዳንዳቸው ምን እንደሚሠሩ በዝርዝር ባናይም፤ የመንፈስ ቅዱስን ድርሻና የሥራ ኃላፊነት ምን እንደ ነበረና እንዴት እንደተወጣው፤ አሁንም በዘመናችን ምን እንደሚሠራ እንመለከታለን፡፡ ሀ) Read more…

መንፈስ ቅዱስ

ሐ) አስተምህሮተ መንፈስ ቅዱስ      1) መንፈስ ቅዱስ ማነው? መንፈስ ቅዱስ ማነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ መጽሐፍ ቅዱስን በሙሉ መዳሰስን ይጠይቃል፤ ቀደም ብለን በአስተምህሮተ እግዚአብሔር እና ክርስቶስ እንደ ተመለከትነው፤ አሁን ደግሞ ስለ አስተምህሮተ መንፈስ ቅዱስ ዘርዘር አድርገን እናጠናለን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከሥላሴ አካላት አንዱና ሦስተኛው አካል እንደሆነ ስለ ሥላሴ ባደረግነው ጥናት መጠነኛ Read more…

መከራው

የክርስቶስ መከራውና ክብሩ ‹‹ጌታችን ኢየሱስ የደረሰበት መከራ እጅግ ከፍተኛ ሲሆን፣ ይህም መሞቱ፣ መቀበሩና ወደ ሲዖልም መውረዱ ነበረ፤ እነዚህን ሁናቴዎች የታገሠውም ሰዎችን ከኀጢአታቸው ለማዳን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ እየተከበረ ሲሄድ ግን በትንሣኤና በዕርገት ሁኔታዎች ዐልፎ በአብ ቀኝ ተቀመጠ፤ እዚያም የዳግም ምጽአቱን ጊዜ ይጠብቃል›› (ትምህርተ ክርስቶስ በቄስ ማንሰል ገጽ 198) ሲሉ መከራውና ክብሩን Read more…

መሲህ

የክርስቶስ አገልግሎት             ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን በአባቱ በወጣው ዕቅድ መሠረት በሦስት የአገልግሎት (ቢሮዎች) ክፍሎች እንደ ካህን፣ ነቢይና ንጉሥ ሆኖ እንደሚያገለግል አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የተነገሩ ትንቢቶች ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት የብሉይ ኪዳን ሰዎች፣ መሲህ ይመጣል ብለው ይጠብቁት እንደ ነበረ፣ የትንቢት መጻሕፍት ሁሉ ዘግበዋል፡፡ በተለይም በኢሳይያስ ምዕራፍ 53 ላይ በስፋት ተነግሮ እንደምናገኘው፣ Read more…

ክርስቶስ

አስተምህሮተ መለኮት (ክርስቶስ)  ቀደም ብለን በአስተምህሮተ ሥጋዌ ባጠናነው ጥናት፣ ኢየሱስ በቅድመ-ህልውናው (Preexistence) በብሉይ ኪዳን ጊዜ በመላእክትና በሰዎች መልክ መገለጡ የመለኮታዊነቱን እርግጠኛነት ማየት ያስችለናል፡፡ በየዘመናቱ ሰዎች የክርስቶስን መለኮታዊነት ቢክዱም መጽሐፍ ቅዱስ ግን አምላክነቱን በግልጽ ያመለክተናል፡፡ ከዚህ በፊት ባጠናናቸው ትምህርቶች ስሞቹ ሰብዓዊነቱንና መለኮታዊነቱን የሚያመለክቱ እንደሆኑ ተመልክተናል፤ ከፍጥረት በፊት አስቀድሞ መኖሩ፣ ከእግዚአብሔር መምጣቱ፣ Read more…

ወልድ

የኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት የሰው አካል ነበረው፡- ኢየሱስ ሰማያዊ አካል እንደ ነበረው፣ እንዲሁ ምድራዊ የሰው አካል ነበረው፡፡  ከማርያም ሥጋ ነስቶ በመወለዱ የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ የሚያንቀላፋ፣ የሚደክም፣ የሚተኛ፣ የሚያለቅስ፣ የሚደሰትና የሚያዝን አካል እንደ ነበረው፤ የሚከተሉት ጥቅሶች ያመለክቱናል፡፡ መራቡን ማቴ.4፡2፣ መጠማቱን ዮሐ. 19፡28፣   መድከሙን 4፡6፣ መታወኩን ዮሐ. 12፡27፣ 13፡21፣ ማዘኑን ማቴ. 26፡38፣ ማልቀሱን ዮሐ. Read more…