የመጨረሻው ፍርድ

ስለ ፍርድ ስናነሳ የተለያዩ ፍርዶች እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ ቀደም ብለን የተመለከትናቸው አመለካከቶች ሁሉም ፍርድ እንዳለ ያምናሉ፡፡ የአመኑም ያላመኑም ሁሉም ፍርድ እንዳአለባቸው በቃሉ ውስጥ እናገኛለን፤ የፍርዱ ዓይነት ግን ይለያያል፡፡ አማኞች በሥራቸው ለሽልማት ሲፈረድባቸው ያላመኑት ደግሞ ባለማመናቸው ምክንያት ፍርዱ ለጥፋትና ለቅጣት ይሆንባቸዋል፡፡      ሀ) የመስቀል ፍርድ፡- መጽሐፍ ቅዱስ ፍርድ ዛሬውኑ እንደሚጀምር Read more…

የሙታን ትንሣኤ

ቀደም ብለን እንዳየነው በሦስቱም አመለካከቶች የሺውን ዓመትና የታላቁ መከራ መኖር አይክዱም፡፡ ነገር ግን በሚፈጸምበት ቦታና ጊዜ ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ በሺው ዓመት ግዛት ውስጥ ነው ያለነው ሲሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ ሺውን ዓመት ጌታ በሰማይ ሆኖ እየገዛ ይገኛል ይላሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ጌታ ገና ወደፊት ሲመጣ  በምድር የሚፈጸም ግዛት ይሆናል ብለው ያምናሉ፡፡ Read more…

የተለያዩ አመለካከቶች

የተለያዩ አመለካከቶች      በክርስቶስ ተመልሶ በመምጣቱና በምልክቶች ብዙዎች ቤተ እምነቶች ቢስማሙም፤ በመከራው ዘመን፣ በሺህ ዓመት ግዛት፣ በሙታን ትንሣኤ፣ በፍርድ፣ በመንግሥተ ሰማይና በገሃነመ እሳት የተለያዩ አመለካከቶች አሉዋቸው፡፡ እነዚህ አመለካከቶች የሚለያዩት ሺህ ዓመት አለና የለም በሚሉት ሐሳቦች ላይ ሲሆን፤ የሺህ ዓመት አገዛዝ ካለ፣ የሚሆነው/የሚፈጸመው ከክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በፊት ነው ወይስ በኋላ? በሚለው Read more…

የመጨረሻው ዘመን

አስተምህሮተ ሥነ-ፍጻሜ (የመጨረሻ ነገሮች) በአስተምህሮተ ሥነ-ፍጻሜ ርዕስ ሥር ስለ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት፣ ስለ መከራው ዘመን፣ ስለ ሺህ ዓመት ግዛት፣ ስለ ሙታን ትንሣኤና ፍርድ የምናይበት ይሆናል፡፡ ወደ ፊት ስለሚፈጸሙ ጉዳዮች ስናነሳ መቶ በመቶ እርግጠኛ የማንሆንባቸው ነገሮች ቢኖሩም፤ ከሃምሳ በላይ እርግጠኞች መሆን እንችላለን፡፡ ‹‹ምንም እንኳ ስለ ወደ ፊቱ ማንኛውንም ማወቅ ባንችልም፣ እግዚአብሔር Read more…

ሥርዓቶች

7.  የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶችን በሁለት ከፍለን እናጠናቸዋለን፤ በጌታ በራሱ የተሰጡና ቤተ ክርስቲያን በልምምድ ካሳለፈችው በመነሳት ያስፈልጋሉ ብላ ያመነችባቸውንና ከቃሉ ጋር አይጋጭም በማለት የተለማመደቻቸውን አካታ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች/ሚስጢራት ብላ በማካሄድ ላይ ትገኛለች፡፡ በጌታ የተሰጡ ሥርዓቶች፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጌታ ተሰጥተው የምናገኛቸው ሥርዓቶች ሁለት ሲሆኑ፤ እነርሱም  ሀ) የውኃ ጥምቀትና Read more…

አባልነት

6 . የቤተክርስቲያ ን አባልነት ስለ ቤተ ክርስቲያን አባልነት ጥናታችንን ስንጀምር፣ የቤተ ክርስቲያን አባልነት የዓለም አቀፏና የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ተብለው በሁለት መከፈላቸውን አስቀድመን ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ቀደም ብለን ስለ ድነት ባየነው ትምህርት መሠረት አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ፤ በኃጢአቱ ተጸጽቶ፤ ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታውና አዳኙ አድርጎ ሕይወቱን ለጌታ በሚሰጥበት ጊዜ Read more…

የቤተ ክርስቲያን መሪዎች

5. የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሀ) ሐዋርያት፡- ስለ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በምናጠናበት ጊዜ የምናገኛቸው መሪዎች፣ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ፣ አገልግሎት እንደ ጀመረ፣ ቀደም ብሎ ሐዋርያትን መርጦ አገልግሎት ማስጀመሩ የሚታወቅ ነው፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተመርጠው ሕይወታቸውን ለጌታ በማስረከብ ተከታዮቹ፣ ደቀ መዛሙርትና አገልጋዮቹ ሆነው በማለፋቸው፤ ከትንሣኤም በኋላ የመሪነቱን ሥፍራ ይዘው Read more…

አጥቢያዊ

4 . አጥቢያዊት ቤተ ክርስቲያን ቀደም ባለው ጥናታችን የቤተ ክርስቲያን ምንነትና ጅማሬ፤ በብሉይና በአዲስ ኪዳን ምን መልክ እንደ ነበራትና ተልዕኮዋን ለመዳሰስ ጥረት አድርገናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን በሁለት መልኳ ዓለም አቀፋዊና አጥቢያዊ በሆነ ሁኔታ ይገልጣታል፤ በማትታይና በምትታይ መልኳ ሰማያዊና ምድራዊ አድርጎ አስቀምጦአታል፡፡ አንዷ የማትታየው ዓለም አቀፏ ቤተ ክርስቲያን በሚታይ መልኳ Read more…

ዓለም አቀፋዊ

3 . ዓለም አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ ባለው መሠረት፣ አንዲት የማትታይ ዓለም አቀፋዊ (UNIVERSAL) ቤተ ክርስቲያን አለችው፡፡ በግሪክኛው አጠራር ቀደም ብለን ‹‹ኤክሌሽያ›› (ተጠርተው የወጡ) ብለን የጠራናት ስትሆን፣  በወንጌል ጥሪ ደርሷቸው ከሰይጣን ወደ ክርስቶስ ግዛት፣ ከጨለማ ወደ  ብርሃን ተጠርተው የወጡ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነውና በደሙ ታጥበው፣ በአንድ ቦታ በአካል Read more…

ቤተ ክርስቲያን

3) አስተምህሮተ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮተ መንፈስ ቅዱስ በሚለው ዋና ርዕሳችን ሥር ስናጠና የቆየነው መንፈስ ቅዱስና ድነት (ደህንነት) የሚሉትን ትምህርቶች ነበር፤ አሁን በመቀጠል የምናጠናው ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ርዕስ ይዘን ጥናታችንን እንቀጥላለን፡፡ የጥናታችን ዋና ዓላማ የየትኛውንም ቤተ እምነት አስተምህሮ ትክክል ነው ወይም ትክክል አይደለም የሚል ሳይሆን፤ የጥናታችን መሠረት የሚሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ Read more…