ቃሉን ስበክ

‹‹የማንን?›› የንባብ ክፍል፡- ገላትያ 1 ‹‹ ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁ? ወይስ ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንኩም›› ቁ. 10 እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን የሚያውቅ፣ በሁሉ ቦታ የሚገኝ፣ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው፣ አልፋና ኦሜጋ የሆነ የሚታዩትን በኅዋና በጠፈር ውስጥ ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ የፈጠረና የሚያዛቸውም አምላክ Read more…

ያድናል

‹‹የተከፈተ በር›› የንባብ ከፍል፡- 1ቆሮንቶስ 16 ‹‹ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛል…›› ቁ. 9 በሰው ልጆች የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሥራ የተቃወሙ ሰዎች እጅግ ብዙ ቢሆኑም አንድ ጊዜም እንኳን ተሳክቶላቸው እግዚአብሔርን ከዘላለማዊ የሥራ ዕቅዱ አውርደውት አያውቁም፡፡ ትውልድ አልፎ ትውልድ ሲተካ እርሱን የሚወዱና የእርሱ አገልጋዮች የሆኑ የሚደርስባቸውን ተቃውሞና ስደት ተጋፍጠው ድል በማድረግ፣ Read more…

የተሰቀለው

‹‹የተሰቀለውን መስበክ›› የንባብ ክፍል፡- 1ቆሮንቶስ 1 ‹‹አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ፣ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፣ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ቁ.22 ጥበብንና እውቀትን ከእግዚአብሔር ነጥሎ ለሚሻ ሰው ወንጌልን መሰበክ እንደ ሞኝነት እንደሚያስቆጥርና ወንጌልም ለማያምኑት ሞኝነት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቁማል፡፡ በሚያምኑት ዘንድ ወንጌል የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ፣ የእውቀት ሁሉ ማኅደር፣ የእውነት ሁሉ ምንጭና የዘላለማዊ Read more…

ሸክም

‹‹የወንጌል ሸክም›› የንባብ ክፍል፡- ሮሜ 9 ‹‹ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለኝ›› ቁ. 1 ሐዋርያው ‹‹‹‹ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት›› በልቡ ውስጥ እንዳለ ይናገራል፡፡ ይህ ኀዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት ቅዠት እንዳይደለ ነገር ግን በተጨባጭ ሁኔታ አብሮት ያለ ነገር እንደሆነ ለማረጋገጥ ሲፈልግ ‹‹በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፣ አልዋሽም፣ ኅሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል›› በማለት ይገልጻል፡፡ Read more…

መሥዋዕትነት

‹‹እስራት›› የንባብ ክፍል፡- የሐዋርያት ሥራ 28 ‹‹… ስለ እስራኤል ተስፋ ይህን ሰንሰለት ለብሻለሁና›› ቁ. 20 ሐዋርያው ጳውሎስ በአይሁድ ሰዎች ስለ ተከሰሰበት ጉዳይ ትክክለኛ ፍርድ እንደማያገኝ ስላመነበት ወደ ቄሣር ይግባኝ ብሎ ስለነበረ ታስሮ የሮማውያን መዲና ወደ ሆነችው ሮም ተወሰደ፡፡ በሐዋርያው በኩል ወደ ሮም እንዲመጣ ምክንያት የሆነው ‹‹ይግባኝ›› ማለቱ ይሁን እንጂ ወደ Read more…

አደራህን ጠብቅ

‹‹አደራን መፈጸም›› የንባብ ክፍል፡- የሐዋርያት ሥራ 20 ‹‹… ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴ በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ›› ቁ. 24 ጳውሎስ በእስያ አያሌ ቀናት ከተቀመጠ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ እንዳሰበ በምዕራፉ ውስጥ እንመለከታለን፡፡ በእስያ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች Read more…

አትፍራ

‹‹በብዙ መከራ›› የንባብ ክፍል፡- የሐዋርያት ሥራ 14 ‹‹ወንጌል ሰብከው ብዙዎችን ደቀ መዛሙርት ካደረጉ በኋላ የደቀ መዛሙርተን ልብ እያጸኑ፣ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል፤ እያሉ ወደ ልስጥራን፣ ወደ ኢቆንዮንም፣ ወደ አንጾኪያም ተመለሱ›› ቁ. 21-22፡፡ ጳውሎስና በርናባስ በዚህ ምዕራፍ እንደምንመለከተው ከነበሩበት ሀገር ተሰደው ወደ ኢቆንዮን Read more…

የመዳን ቃል

‹‹ብትቃወም ይብስብሃል›› የንባብ ክፍል፡- የሐዋርያት ሥራ 9 ‹‹አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፣ የመውጊያውን ብረት በትቃወም ለአንተ ይብስብሃል›› ቁ. 5 መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት በአይሁድ አገር እርሻ በሚያርሱበት ጊዜ አንድ የሚያደርጉት ነገር አለ፡፡  የሚያርሱበት በሬ በጣም ኃይለኛ ሆኖ የሚዋጋና የሚፈራገጥ ከሆነ፣ የሚያሰለጥኑበት ዘዴ አላቸው፡፡ በሬውን በተለያዩ ዘዴ ይዘው ከጠመዱት በኋላ እየተራገጠ ሲያስቸግርና Read more…

ተዘጋጅ

‹‹ለመናቅ››                                                       የንባብ ክፍል፡- የሐዋርያት ሥራ 5 ‹‹… ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ›› ቁ. 41 ስለ ስሙ መነቀፍ፣ በመከራና በስደት ውስጥ ማለፍ የእያንዳንዱ እውነተኛ ክርስቲያን ጽዋ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ የነበረውን ተልዕኮ በብዙ መናቅና ስደት እስከ ሞት ድረስ የታመነ በመሆን የአባቱን Read more…

አላፍርም

በባለፉት ወራቶች ከመና የጸሎት መመሪያ ‹‹ዘመንን ስለ መዋጀት፣ ስለ ክርስቶስ ልደት ስለ ትንሣኤውና ወደ አባቱ ስለ መሄዱ ተመልክተን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በ‹‹ወንጌል አላፍርም›› በሚል በተከታታይ በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት  ላይ ተመሥርተን እንመለከታለን፤ ጌታ እንዲያስተምራችሁ በጸሎት ሆናችሁ አንብቡት፡፡ ‹‹እመሰክርለታለሁ››  የንባብ ክፍል፡ ማቴዎስ 10  ‹‹በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ Read more…