ሰይጣን

3.2 የወደቁ መላእክት 2፡1 ሰይጣን፡- በባለፈው ጥናታችን መላእክት ያልወደቁ የወደቁት ብለን ተመልክተናል፤ አሁን በመቀጠል በወደቁ መላእክት ላይ ትኩረታችንን እናደርጋለን፡፡ መላእክት አስቀድሞ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ የከበሩ መላእክት ነበሩ፡፡ ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው ምክንያት የማገልገላቸውን መብትና ክብር አጡ፡፡ ስለ ወደቁ መላእክት ስንመለከት ያልታሰሩና የታሰሩ መላእክት ብለንበሁለት ከፍለን እንመለከታቸዋለን፡፡ ስለ ውድቀታቸው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሁሉ በተቻለ Read more…

የመላእክት አገልግሎት

የመላእክት ሥራቸው፡- ስለ መላእክት ማንነታቸውንና ስሞቻቸውን ከዚህ ቀደም ብለን የተመለከትን  ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በክርስቶስና በአማኞች ሕይወት የሰጡትን አገልግሎትና ሥራ እናጠናለን፡፡ መላእክት የማይታዩ ከሆነ ሥራቸውን ማን ሊመለከት ይችላል ተብሎ የሚጠየቅ ጥያቄ ሊኖር ይችላል? እኛ ሥራቸውን አየን አላየን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሥራ እንዳላቸው ከነገረን መቀበል አለብን፡፡ ስለዚህ መላእክት እግዚአብሔርን ከማገልገል ውጭ የተለያዩ ሥራዎች Read more…

መላእክት

አስተምህሮተ መላእክት ያልወደቁ መላእክት በቀደመው ጥናታችን የተመለከትነው አስተምህሮተ እግዚአብሔር የሚል ነበር፤ በመቀጠል የምንመለከተው አስተምህሮተ መላእክት የሚለውን ሦስተኛውን ርዕሳችንን ይሆናል፡፡ ስለ መላእክት መፈጠር ስናጠና መቼ እንደ ተፈጠሩ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ምንም ሥፍራ የለውም፡፡ መላእክት እግዚአብሔር  ከፈጠራቸው ፍጥረታት መካከል አንዱ መሆናቸው ቃሉ ስለሚነግረን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ሰዎች  የመላእክትን መኖር ቢያምኑም ባያምኑም  እርግጠኛ Read more…

ሥላሴ (ክፍል 2)

ወልድ፡- ‹‹እግዚአብሔር ወልድ››  ከሥላሴ አካል አንዱ ሲሆን፤  የሰው ልጆችን ለማዳን ወደዚህ ምድር ከድንግል ማርያም ሥጋ ነስቶ በመምጣትና ለኃጢአታችን በመስቀል ላይ በመሞት ከአባቱ ጋር ያስታረቀን ወልድ ነው፡፡  ሐዋርያው ጳውሎስ በቲቶ መልእክቱ ምዕራፍ 1፡1-4 ባለው ክፍል ላይ  ‹‹… የማይዋሽ እግዚአብሔር(አብ) ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ፣ በዘመኑም ጊዜ፣ መድኃኒታችን እግዚአብሔር (ወልድ) እንዳዘዘ፣ ለእኔ Read more…

ሥላሴ (ክፍል 1)

  የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ባለፈው ጥናታችን ያጠናነው የእግዚአብሔርን መጠሪያ ስሞች ሲሆን በመቀጠል የምናጠናው የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት ስለሚገልጠው ሥላሴ ይሆናል፡፡ በቄስ ማንሰል ስለ ሥላሴ እንዲህ ይላሉ ‹‹በአንዱ እግዚዘብሔር ዘንድ ሦስትነት አለ፤ በመካከላቸው ‹‹እኔ … አንተ… እርሱ›› የሚል አጠራር አለ፡፡ እግዚአብሔር የአስተርእዮን (መገለጥን) ተግባር ወደ ፍጻሜ ሲያደርሰው፣ ልጁንና መንፈሱን ወደ ዓለም በመላክ Read more…

የእግዚአብሔር መጠሪያ

2.4 የእግዚአብሔር መጠሪያ ስለ አስተምህሮተ እግዚአብሔር ስንጀምር፣ የእግዚአብሔር መኖር በሚለው ርዕስ ሥር እንደተመለከትነው፣ ቃሉ ከሁለት ጥምር ከሆኑ የግዕዝ ቃሎች የመጣና ትርጉሙም ‹‹የሕዝቦች ጌታ›› ማለት እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ ይህ በአማርኛችን ሲሆን፣ በመቀጠል እግዚአብሔር የሚለውን መጠሪያ ስም በመሠረታዊ ቋንቋው እንመለከተዋለን፡፡ ብሉይ ኪዳን በተጻፈበት በዕብራይስጥ ቋንቋ ስናጠና ስም መለያ፣ መጠሪያና የማንነት መገለጫ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ Read more…

የእግዚአብሔር ባሕርያት (ክፍል 5)

3.13 ፈራጅ ነው፡- በዚህ በመጨረሻው የእግዚአብሔር ባሕርያት ጥናታችን የምንመለከተው የእግዚአብሔርን ፈራጅነት፣ በሁሉ ሥፍራ መገኘትና አለመለወጡን እንመለከታለን፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት ስለ እግዚአብሔር ፈራጅነት ሲናገር ‹‹የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው›› በማለት ሚዛናዊ አምላክ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ፍርዱ የተመሠረተው በቅንነቱ፣ በእውነቱና በጻድቅነቱ ላይ ነው (መዝ. 19፡9)፤ መዝሙረኛው በሌላም ሥፍራ ‹‹እግዚአብሔር መሓሪና ጻድቅ ነው›› (መዝ.116፡5) Read more…

የእግዚአብሔር ባሕርያት (ክፍል 4)

3.10 ሁሉን አዋቂ ነው፡- ባለፈው ጥናታችን እግዚአብሔር ዘላለማዊ፣ ፍቅርና ነፃ መሆኑን ተመልክተን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ፣ ሁሉን ቻይና ከሁሉ በላይ መሆኑን በጥናታችን እንመለከታለን፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው፣ ስንል ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን፣ ዛሬም ያለውን፣ ወደ ፊትም የሚመጣውን ሁሉ ያውቃል፡፡ ዛሬ ብዙ ሳይንቲስቶችና ጠበብት ባሉበት አገር ዓለም በኮቢድ 19 Read more…

የእግዚአብሔር ባሕርያት (ክፍል 3)

3.7 ዘላለማዊ ነው፡- መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ዘላለማዊነት ሲገልጽ፤ የዘፍጥረት መጽሐፍ 1፡1 ላይ ሲጀምር ‹‹በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ›› ይላል፡፡ በመጀመሪያ በሚልበት ጊዜ መጀመሪያውና መጨረሻው መቼ እንደሆነ በፍጹም ባይታወቅም፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ የዘላለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም እንደ ጠራ ይነግረናል (ዘፍ.21፡33)፡??፡ ሙሴም በመዝሙሩ ‹‹ተራሮች ሳይወለዱ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ Read more…

የእግዚአብሔር ባሕርያት (ክፍል 2)

3.4 አይወሰንም፡- ከዚህ ቀደም ብለን ባለፈው ጥናታችን እንደ ተመለከትነው፤ እግዚአብሔር ኃያል በመሆኑና ሰው ባለመሆኑ በምንም ነገር አይወሰንም፡፡ ዳዊትም በመዝሙሩ ‹‹እግዚአብሔር ታላቅ ነው፣ … ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም፡፡ ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፣ ኃይልህንም ያወራሉ›› (መዝ. 145፡3-4) በማለት ሲገልጸው፤  ሐዋርያው ጳውሎስም ‹‹ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ Read more…