የተገለጠ ቃል

1. 3 የቃሉ መገለጥ  3.1መገለጥ ምንድን ነው ?   መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር መገለጥ ቢሆንም፣ ወንድም ምኒልክ እንዲህ ይላሉ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ቋንቋ የተጻፈ የእግዚአብሔር ሥልጣናዊ ቃል ነው›› ትርጉሙንም እንዲህ አስቀምጠውታል ‹‹መገለጥ መከሰት፣ መታወቅ፣ መታየት፣ በዚሁም መገኘት ማለት ነው›› (መጽሐፍ ቅዱስና የትርጓሜ ስልቱ ምኒልክ አስፋው ገጽ 51፣ 53) እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆች Read more…

ቃል ኪዳን

2 ቃል ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ የቃል ኪዳን መጽሐፍ ነው፤ ቃል ኪዳኑም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የተደረገ ሲሆን፣ ከግለሰቦችና ከሕዝቦች ጋር ያደረገው ስምምነት እንደ ሆነ ከተጻፈው ቃሉ ማግኘትና መረዳት እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የመጣውና የተገለጠው በየጊዜው በሚያድግ መገለጥ (Progressive Revelation) እንደ ሆነ፣ ከሰዎች ጋር ባደረገው ቃል ኪዳን አማካኝነት ማየትና መረዳት ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር በብሉይ Read more…

መጽሐፍ ቅዱስ

ሀ) አስተምህሮተ እግዚአብሔር     1) አስተምህሮተ መጽሐፍ ቅዱስ መግቢያ፡- በዚህ አስተምህሮተ እግዚአብሔር በሚለው ርዕስ ሥር አስቀድመን የምናጠናው፤ ስለ አስተምህሮተ መጽሐፍ ቅዱስ ይሆናል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ  ስለ እግዚአብሔር  መገለጥ (Revelation) የሚገልጽና የሚያስረዳ መጽሐፍ በመሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በመንፈስ ቅዱስና በሰዎች ሆኖ የተናገረው የራሱ ቃል ስለ ሆነ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ስለ እግዚአብሔር Read more…

መግቢያ / አስተምህሮ

ክርስታናዊ አስተምህሮን ወይም መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮን (ዶክትሪን) ለመጻፍ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች መጽሐፍ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር፣ ክርስቶስ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ ድነት፣ ቤተ ክርስቲያን፣ መላእክት፣ የመጨረሻው ዘመን እያሉ ርዕስ ሰጥተውና ከፋፍለው አልጻፉትም፤ ምክንያቱም ጸሐፊዎቹ በየዘመናቱ ለተነሱ ችግሮች የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ እየሰሙ መፍትሔ ለመስጠት በጽሑፍ የወሰዱትን ርምጃ ነው፣ በቃሉ ተጽፎ የምናገኘው፡፡ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትንና ያልተዘረዘሩት Read more…

የዘመናት እውነት (ክፍል አራት)

እኔ የዛሬ ሠላሳ አምስት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ በኢቲሲ ስማር፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ/ ትምህርት የሚረዱ የአማርኛ መጽሐፍት አልነበሩም፤ ትምህርት ካቆምኩኝ ጥቂት ዓመታት አልፈው ስለነበረ፣ እንግሊዝኛው ለእኔ ላቲን ሆኖብኝ ነበር፡፡ በተቻለ መጠን በመፍጨርጨርና ጊዜ በመስጠት፣ በአስተማሪዎችም ዕርዳታ ትምህርቱን መከታተል ቻልኩኝ፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን በዚያው ዓመት የማታ መጽሐፍ ቅዱስ ትምሀርት Read more…

Happy Ethiopian New Year

ውድ የተልዕኮ ኦን ላይን አገልግሎት ተከታታዮች ላለፉት ሁለት ዓመታት ተልዕኮ teleko.org በሚለው ድህረ ገፅ እና የሶሻል ሚዲያ ቴሌግራምና ፌስ ቡክ ተከታታይ የሆኑ ጽሑፎችንና ትምህረቶችን ስናጋራ ቆይተናል፡፡ ‹‹አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፣ አቤቱ፡- ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ፡፡ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፣ ተቆጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፣ አትጣለኝ፣ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፣ Read more…

የዘመናት እውነት (ክፍል ሦስት)

የዛሬውን ጥናት ከማየታችን በፊት፣ በባለፈው ሳምንት የተሠጠውን የምንባብ ክፍል የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15፡36-41 ባለው ክፍል ውስጥ በእኛና በቤተክርስቲያን መካከል  ስላለው ግንኙነት ምን እንደ ተማርንበት እንመልከት፡፡ ‹‹… ስለዚህ እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፣ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ፡፡ ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፣ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ Read more…

የዘመናት እውነት (ክፍል ሁለት)

በዛሬው ጥናታችን የምንመለከተው ክፍል የኤፌሶን መልእክት ምዕራፍ 5፡21-33 ይሆናል፤ ከዚያ በፊት አስቀድመን  በባለፈው የተሰጠውን የጥናት ክፍል ምን እንደ ተማርንበትና በተግባር ልናውለው የሚገባንን አብረን እንይ፡፡ የጥናት ክፍላችን የነበረው የሉቃስ ወንጌል 2፡41-52 ነበር፣ በተግባር የምታውሉት ምን ትምህርት አገኛችሁበት?           በዚህ ክፍል ወላጆችም ልጆችም የምንማረውና በተግባር ልናውላቸው የሚገቡ ብዙ ቁም ነገሮች አሉ፡፡ በቁጥር Read more…

የዘመናት እውነት (ክፍል አንድ)

አብርሃም ልጁን እንዲሠዋ በእግዚአብሔር መታዘዙን ከሕይወታችሁ ጋር አዛምዱት? በተግባር ግለጡት? የሚለውን ይህን አንድ ክፍል ወስደን በተማርነው መሠረት እየተመለከትን፣ እየተረጐምን ከሕይወታችን ጋር አዛምደን ተግባራዊ ለማድረግ በምትጀምሩበት ጊዜ ቀላል ሆኖ አገኛችሁት?፡፡ ዘፍጥረት ምዕራፍ 22 ቁጥር 2 ላይ ‹‹ … የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ Read more…

ማዛመድ

በመጀመሪያ ለጥናት የተሰጠው ክፍል የሚገኘው ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28፡19-20 ላይ ነበር፡፡ በዚህ ክፍል ጌታ  ስለ ጥምቀት የሰጠውን ትእዛዝ፣ ጴጥሮስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2፡38 ላይ ‹‹…በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ›› ብሎ ማስተማሩ በጌታ የተሰጠውን ትእዛዝ መለወጡ አይደለም፡፡ ‹‹ንስሐ ግቡ፣ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ›› ብሎ Read more…