የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን አሁን በስፋትና በዝርዝር የማየት ዓላማ የለንም፣ ማጥናት ለምንፈልግ  ግን እንድናጠናው የሚያስችሉንን የመጽሐፉን ውቅር ልንከፋፍል እንችልበታለን ብዬ እኔ ያመንኩበትን ሦስት አካሄዶችን አቅርቤላችኋለሁ፣ ተጠቀሙበት፡፡ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ሦስት አከፋፈሎች፡-

1. በሰዎች ታሪክ   ሀ. ጴጥሮስ  ምዕ. 1 – 12

      ለ. ጳውሎስ ምዕ. 13- 28  

2. በስፍራ (ጂኦግራፊያዊ) አቀማመጡ   

    ሀ. ኢየሩሳሌም   ምዕ. 1-7 

   ለ. ይሁዳ        ምዕ  . 8-12 

  ሐ. ሰማርያ      ምዕ . 8-12   

  መ. ዓለም       ምዕ. 13-28

3. በጸሐፊው አከፋፈል

 ሀ. ምዕ .1፡1- 6፡7 – ወንጌል በኢየሩሳሌም

 ለ. ምዕ. 6፡8- 9፡31 – ወንጌል በይሁዳና በሰማሪያ

 ሐ. ምዕ. 9፡32- 12፡24 – ወንጌል በዓለም ዳርቻ

 መ. ምዕ. 12፡25- 16፡5 –   ››      ››

 ሠ. ምዕ. 16፡6- 19፡20 –  ››       ››

ረ. ምዕ. 19፡21- 28፡31 –  ››       ››

ከዚህ በላይ ያሉትን የመጽሐፉን አከፋፈሎች ስንመለከት፣ ጸሐፊው ጽሑፉን የሚገታውና እንደገና የሚጀምረው የእግዚአብሔር ሥራ እንደ ሠፋና ብዙ ሰዎች ወደ ጌታ መምጣታቸውን ከገለጸ በኋላ ነው፡፡ ሦስተኛው አከፋፈል  ከኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ፣ ወደ ሰማርያና ወደ ቀሩት የዓለም ዳርቻ ወንጌል እንዴት እንደ ሰፋ የገለጸበት መንገድ የውስጥ አከፋፈሉን ያሳየናል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ(አተረጓጐም) መመልከት፣ መተርጐምና ማዛመድ(ከሕይወት ጋር) የሚሉት የተጻፈውን ቃሉን ለመረዳት የሚያስችሉን መንገዶች ናቸው፡፡ በዚህ መልክ ጽሑፉን ስንመለከተው፣ የጸሐፊው ዋና ዓላማና ትኩረት የት ላይ እንደሆነ ለመረዳት ለጽሑፉ የሰጠውን መጠን (proportion) ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ዋናው ትምህርት ቀስ በቀስ መግባት እንጀምራለን፡፡


0 Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *