ሸክም

‹‹የወንጌል ሸክም›› የንባብ ክፍል፡- ሮሜ 9 ‹‹ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለኝ›› ቁ. 1 ሐዋርያው ‹‹‹‹ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት›› በልቡ ውስጥ እንዳለ ይናገራል፡፡ ይህ ኀዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት ቅዠት እንዳይደለ ነገር ግን በተጨባጭ ሁኔታ አብሮት ያለ ነገር እንደሆነ ለማረጋገጥ ሲፈልግ ‹‹በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፣ አልዋሽም፣ ኅሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል›› በማለት ይገልጻል፡፡ Read more…

መሥዋዕትነት

‹‹እስራት›› የንባብ ክፍል፡- የሐዋርያት ሥራ 28 ‹‹… ስለ እስራኤል ተስፋ ይህን ሰንሰለት ለብሻለሁና›› ቁ. 20 ሐዋርያው ጳውሎስ በአይሁድ ሰዎች ስለ ተከሰሰበት ጉዳይ ትክክለኛ ፍርድ እንደማያገኝ ስላመነበት ወደ ቄሣር ይግባኝ ብሎ ስለነበረ ታስሮ የሮማውያን መዲና ወደ ሆነችው ሮም ተወሰደ፡፡ በሐዋርያው በኩል ወደ ሮም እንዲመጣ ምክንያት የሆነው ‹‹ይግባኝ›› ማለቱ ይሁን እንጂ ወደ Read more…

አደራህን ጠብቅ

‹‹አደራን መፈጸም›› የንባብ ክፍል፡- የሐዋርያት ሥራ 20 ‹‹… ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴ በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ›› ቁ. 24 ጳውሎስ በእስያ አያሌ ቀናት ከተቀመጠ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ እንዳሰበ በምዕራፉ ውስጥ እንመለከታለን፡፡ በእስያ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች Read more…

አትፍራ

‹‹በብዙ መከራ›› የንባብ ክፍል፡- የሐዋርያት ሥራ 14 ‹‹ወንጌል ሰብከው ብዙዎችን ደቀ መዛሙርት ካደረጉ በኋላ የደቀ መዛሙርተን ልብ እያጸኑ፣ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል፤ እያሉ ወደ ልስጥራን፣ ወደ ኢቆንዮንም፣ ወደ አንጾኪያም ተመለሱ›› ቁ. 21-22፡፡ ጳውሎስና በርናባስ በዚህ ምዕራፍ እንደምንመለከተው ከነበሩበት ሀገር ተሰደው ወደ ኢቆንዮን Read more…

የመዳን ቃል

‹‹ብትቃወም ይብስብሃል›› የንባብ ክፍል፡- የሐዋርያት ሥራ 9 ‹‹አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፣ የመውጊያውን ብረት በትቃወም ለአንተ ይብስብሃል›› ቁ. 5 መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት በአይሁድ አገር እርሻ በሚያርሱበት ጊዜ አንድ የሚያደርጉት ነገር አለ፡፡  የሚያርሱበት በሬ በጣም ኃይለኛ ሆኖ የሚዋጋና የሚፈራገጥ ከሆነ፣ የሚያሰለጥኑበት ዘዴ አላቸው፡፡ በሬውን በተለያዩ ዘዴ ይዘው ከጠመዱት በኋላ እየተራገጠ ሲያስቸግርና Read more…