የእግዚአብሔር ባሕርያት (ክፍል 2)

3.4 አይወሰንም፡- ከዚህ ቀደም ብለን ባለፈው ጥናታችን እንደ ተመለከትነው፤ እግዚአብሔር ኃያል በመሆኑና ሰው ባለመሆኑ በምንም ነገር አይወሰንም፡፡ ዳዊትም በመዝሙሩ ‹‹እግዚአብሔር ታላቅ ነው፣ … ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም፡፡ ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፣ ኃይልህንም ያወራሉ›› (መዝ. 145፡3-4) በማለት ሲገልጸው፤  ሐዋርያው ጳውሎስም ‹‹ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ Read more…

የቃሉ ኃይል

6.5 የቃሉ ኃይል ቀደም ባለው ጥናታችን ቃሉን አስፈላጊነት ተመልክተናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ አስፈላጊ የነፍሳችን ምግብ መሆኑንም አይተናል፡፡ ቃሉ ምግብ ብቻ ሳይሆን ኃይልም እንዳለው ቀጥለን እንመለከታለን፤ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰማ ሕይወቱ ይለውጣል፤ ምክንያቱም  ቃሉ ኃይል ስለ አለው ነው፡፡ ኢሳይያስ የቃሉን ኃያልነት ሲገልጽ በትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 55፡11 ላይ እንዲህ ይላል፣ Read more…

የቃሉ አስፈላጊነት (ክፍል 2)

የፍቅር መልእክትነቱ በቀደመው ጥናታችን የመጽሐፍ ቅዱስን አስፈላጊነት ተመልክተናል፤ አሁንም በዚህ ጥናታችን ጨምረን የቃሉን አስፈላጊነት እናጠናለን፡፡ እግዚአብሔር ለሰዎች በየዘመናቱ፣ ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ ራዕይ ድረስ ያለውን ስንመለከት አጠቃላይ መልእክቱ የፍቅር ደብዳቤ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እግዚአብሔር ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር በየጊዜው ለሰው ልጆች የላከው መልእክት እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ሰው ባለመታዘዙ ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ጤናማ Read more…

የቃሉ አስፈላጊነት (ክፍል 1)

የመጽሐፍ ቅዱስ አስፈላጊነት  6.1 የቃሉ አንድነት ባለፈው ጥናታችን መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ተመለክተን ነበር፤ እውነተኛ የአምላክ ቃል ከሆነ፤ ለእኛ አስፈላጊያችን መሆኑን በዚህ ጥናታችን እንመለከታለን፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን አስፈላጊነት በስፋት ከማየታችን በፊት፣ አስቀድመን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አንድነት እንመልከት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይና አዲስ ኪዳን ተብሎ በሁለት ክፍል መከፈሉንም ቀደም ብለን ተመልክተናል፡፡ Read more…

እውነተኛ ቃል

1.5 እውነተኛ ቃል የእግዚአብሔር ቃል ከሰዎች ቃል ሁሉ የበለጠና የላቀ እውነተኛና ታማኝ ቃል ነው፡፡ እግዚአብሔር በየዘመናቱ  ለሰዎች የተናገረውን ሲፈጽም የኖረ፤ አሁንም እየፈጸመ የሚገኝ፤ ወደ ፊትም እየፈጸመ የሚኖር አምላክ ነው፡፡ እኛ ፍጥረቶቹ የሆንን ሰዎች እንኳን በምንነጋገራቸው እውነተኛና ታማኝ ቃሎች አማካይነት እርስ በርሳችን በመተማመን መልእክት እንለዋወጣለን፣ ሀሳብ ለሀሳብ እንግባባለን፤ ገንዘብ እንኳን ሳይቀር Read more…