‹‹ተልዕኮው የት ደርሷል?›› የሚለው መጽሐፍ የሐዋርያት ሥራን አጠቃላይ ይዘት የሚያስጨብጥና የኢየሩሳሌምና የአንጾኪያ አብያተ ክርስቲያናት በማነፃፀር ብርታታቸውንና ድካማቸውን ያሳየናል፡፡ ጽሑፉ ተነባቢ ነው፣ በየመሐሉ ያሉት ምሳሌዎቹ ጽሑፉን ሳንሰለች እንድናነበው ያደርገናል፡፡ መጽሐፉ በግላቸው መጽሐፍ ቅዱስን ለሚያጠኑ፣ ለወንጌል አገልጋዮችና ለመጽሐፍ ቅዱስ አስጠኝዎች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
ዶ/ር መጋቢ ስለሺ ከበደ ኢትዮጵያ ገነት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ
በብርቱው ጥርት ባለ ተልዕኮ የተጓዘችው የመጀመሪያቱ ቤተ ክርስቲያን የዚህ ሁሉ ዘመናት ጉልህና ሞዴል ሆና ዘለቀች፡፡ ወ/ዊ አምበርብር ከረጅም ዘመን አገልግሎቱና ከራሱ ሕይወት ጋር አያይዞ ከዚህች ማኅበር አካሄድ የቀዳውን ትምህርት ለአሁኗ ቤተ ክርስቲያን አቅርቧል፡፡ ጽናቱንና ለአገልግሎቱ ያለውን ትጋት አደንቃለሁ፡፡ ሕያው ጌታ የሚወዳትንና የሚጠብቃትን ቤቱን፣ እኛም በነቃ ልብና በአተኮረ ዓይን፣ ለተልዕኮ ዝግጁ በሆኑ እግሮችም ልንመላለስባት ተጠርተናል፡፡
ወንድም ንጉሤ ቡልቻ ኮምፓስ ኢትዮጵያ
‹‹ተልዕኮው የት ደርሷል?›› የሚለው መጽሐፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት አንዱ የሆነውና በተለምዶ የሐዋርያት ሥራ ተብሎ የሚጠራውን መጽሐፍ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያዎቹ የአዲስ ኪዳን ዓመታት ከሠራቸው ሥራዎች ውስን የሆኑትን የሚተርክ ነው፡፡ በማስተማር ችሎታው እኛ ተማሪዎቹ የምንመሰክርለት ወንድም አምበርብር ገብሩ ይህንን መጽሐፍ በሌላ መልኩ አብራርቶ አቅርቦልናል፡፡ መጽሐፉን ሳነብ ወንድም አምበርብር ከመድረክ ላይ ሆኖ የሚናገር ይመስላል፡፡ ይህንን እንድል ያስቻለኝ የተጠቀመባቸው አንዳንድ ቃላትና ሐሳቡን ያቀረበበት መንገድ ነው፡፡ በአንባቢው ልብ ቁጭትንና እልህን የሚጨምር ነው፡፡ በተጨማሪም በወቅቱ የነበሩትን የታላቁን ተልዕኮ ተግዳሮቶችን በዘመናችን ከሚታዩ የተልዕኮው ተግዳሮቶች ጋር አያይዞ በማቅረቡ የመጽሐፉን ሕያውነት ተመልክቻለሁ፡፡ የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን የጀመረችው የሚስዮናዊነት አገልግሎት በተገቢው ሁኔታ ባለመቀጠሉ የተፈጠሩ ክፍተቶችን አሳይቶ፣ የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን የሚስዮናዊነቷን አገልግሎት እንደሚገባ እንደተወጣች በግልጽ አስቀምጦአል፡፡ መጽሐፉ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እስከ ሞት ድረስ በታመኑ ምእመናንና አገልጋዮች እየተተከለችና እየሰፋች እንደምትሄድ፣ እንዲሁም የተቀበሉትን አደራ የማይወጡ ምእመናንና አገልጋዮች በተነሡባቸው ዘመናት ዕድገቷ እየቀጨጨ እንደሚሄድ በግልጽ ያሳያል፡፡ አንባቢዎች ከዚህ መጽሐፍ የሚስዮናዊነት አገልግሎት የሚያስከፍለውን ዋጋ ይገነዘባሉ ብዬ አምናለሁ፡፡
ወንድም ተክሉ ወልዴ የአሥር/አርባ አገልግሎት አስተባባሪ
ብዙዎች የሐዋርያት ሥራ ማብራሪያ የወንጌል ተልዕኮ እንቅስቃሴን ጠቅሰው የጻፉ ቢሆንም ‹‹ተልዕኮው የት ደርሷል?›› የሚለው መጽሐፍ ግን በአቀራረቡ የተለየ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ልዩ የሚያደርገው ከሕይወት ምስክርነት ጋር መያያዙ፣ በሐዋርያት የወንጌል የማስፋፋት አገልግሎት ጋር ብቻ ማተኮሩ፣ የመንፈስ ቅዱስ ምሪትን መቀበላቸውንና መመራታቸውን አጉልቶ ማሳየቱ፣ ለዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ጆሮዎቿን ለመንፈስ ቅዱስ መስጠትና መስማማት እንደሚገባቸው ማመላከቱና የወንጌል ተልዕኮው የወንጌላውያን ወይም የአገልጋዮች ብቻ ሳይሆን፣ በስሙ ተጠርተው ብርሃን የበራላቸው ሁሉ መሆኑን ነው፡፡ ጸሐፊው ጌታ እንዲጽፍ ካስነሣው ብዙ ዕንቁዎች በውስጡ እንዳሉ መመስከርና ሲወጡ ለብዙዎች እንደሚጠቅሙ ከዚህ መጽሐፍ መረዳት ችያለሁ፡፡
እህት ዓይናለም አበበ የት.መ.ማ መሪ/አስተባባሪ
‹‹ተልዕኮው የት ደርሷል?›› የሚለው መጽሐፍ እጅግ በጣም ጥሩ መጽሐፍ ነው፡- አስገራሚ ዕይታ(Observation)፣ ትርጓሜ (Interpretation) እና የሚገባ ለዚህ ዘመንና ትውልድ የሆነ አጠቃቀም (Application) እየገለጸ፣ የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን ለእኛዋ ቤተ ክርስቲያን የሚያስረዳ ‹‹ክርስትና 101›› የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡
ሩሃማ ገዛኸኝ በኢ.ቲ.ሲ ሪጂስትራል/ሌክቸረር
መጽሐፉ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ታሪክ ዋና ጭብጥ ባጭሩ ከማስቀመጡ ባሻገር፣ ክርስቲያኖችን ለወንጌል ኣገልግሎት (ታላቁ ተልዕኮ) የሚያነሳሳ ነው፡፡
ዘካርያስ ሳንታ አ.አ ገነት ክልል ጽ/ቤት
በመጀመሪያ ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍ ላስጀመረኝ፣ አስጀምሮም ላስጨረሰኝ ለእግዚአብሔር ትልቅ ምሥጋና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አቀርባለሁ፡፡ በመጨረሻም ይህን ጽሑፍ በመጽሐፍ (hard copy) ለማግኘት ለምትፈልጉ በኤስ ኣይ ኤም ሥነ ጽሑፍ ክፍልና በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ታገኙታላችሁ፡፡
1 Comment
BennyRot · October 15, 2021 at 10:15 am
Free deep throat porn for you! –> http://trueweightloss.iceiy.com
Free porn Detail : Free porn