ለውጥ ተኮር ውይይት

ባለፈው ትምህርታችን እንደ ተመለከትነው፣ ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ሁለቱን ቡድኖች አስወጥተው ውይይት አደረጉ፡፡ በውይይቱም መካከል ጴጥሮስ ተነስቶ ወደ አሕዛብ (ቆርኔሌዎስ) ቤት ሄዶ እንዲያገለግል እንዴት እንደ ተመረጠና እግዚአብሔርም ሳያዳላ መንፈስ ቅዱስን ለአይሁድ (ሐዋርያት) እና ለአሕዛብም (ቆርኔሌዎስ) እንደ ሰጠ መሰከረላቸው (ቁ.6-11)፡፡ ከዚያም በኋላ እንደገና ጳውሎስና በርናባስ ዕድል ተሰጥቷቸው ለሕዝቡ (ለጉባኤው) ሲያስረዱ ሁሉም ጸጥ ብለው Read more…

የውስጥ ችግር

በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን በምግብ እደላው፣ ገንዘብ በመደበቁ፣ ከአይሁድ ውጭ ወንጌሉን ያለመናገር፣ አሕዛብ የሆኑትን አማኞች ካልተገረዛችሁ እያሉ የሚያስተምሩ ሰዎች መኖራቸውና ማስቸገራቸው አንሶ፤ አሁን ደግሞ ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ወርደው በሰላም የወንጌልን ሥራ የምትሠራውን ቤተ ክርስቲያን ወደ ሙሴ ሥርዓት ካልተመለሳችሁ እያሉ ማስቸገር ጀመሩ፡፡ በሐዋርያት ሥራ 15፡1-2 ላይ እንዲህ ይላል፣ “አንዳንዶችም ከይሁዳ Read more…

ለመጀመሪያ ጊዜ

ጳውሎስ ዜግነቱን ብቻ ሳይሆን፣ በገማልያል እግር ሥር ቁጭ ብሎ የተማረውን ትምህርቱን ተጠቅሞበታል፡፡ እኔ እንደ ምረዳውና የሐዋርያት ሥራን ሳጠና እንዳገኘሁት፣ በኢየሩሳሌም የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን እስከ አሥር ዓመት ድረስ የመሯት ሐዋርያት ነበሩ፡፡ ምክንያቱም እሰከ ምዕራፍ 11፡1 ድረስ ሽማግሌዎች የሚል ቃል ተጠቅሶ አናገኝም፡፡ ከምዕራፍ 11፡30 ላይ ስንደርስ ግን በርናባስና ጳውሎስ ከአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን Read more…

መልዕክት ላኪ እና ተቀባይ

እነ ጳውሎስ በአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያገለገሉ ሳለ፣ የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ከደረሳቸው በኋላ ለወንጌል አገልግሎት ፈቃደኛ ሆነው ራሳቸውን  ለይተው ሲውጡ፣ ሉቃስ በጽሑፉ ይተርክልናል፡፡ በምዕራፍ 13፡4 ላይ ስንመለከት፣ “እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄዱ” ይላል፡፡ በመቀጠልም፣ ወደ ስልማናም ከዚያም ወደ ተለያዩ ከተማዎች እንደ ሄዱ እንመለከታለን፡፡ Read more…

ተልዕኮን ማሳካት

የአንጾኪያን ቤተ ክርስቲያን ስንመለከት፣ ጸሐፊው መተረክ የሚጀምርልን በአጥቢያይቱ በነበሩት አገልጋዮች ላይ ይሆናል፡፡ በሐዋርያት ሥራ 13፡1 ላይ አምስት ያህሉን ሰዎች በስም በመጥቀስ ከሚዘረዝራቸው መካከል በርናባስና ጳውሎስ ይገኙበታል፡፡ በመቀጠልም፣ በዚህች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የጾምና ጸሎት ጊዜ እየተካሄደ መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ ብሎ እንደ ተለዩ፣ በተለይም ለሚስዮናዊነት አገልግሎት እንደተጠሩና የመጀመሪያውን Read more…

አዲስ ጅማሬ

በሰው ሕይወት አዲስ ነገር መጀመር በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፣ በተለይም በዕድሜ እንደ እኔ ገፋ ላደረጉ ሰዎች በጣም ይከብዳል፡፡ ከለመድነው የአሠራር መንገድ ለወጥ ለማድረግ፣ ሥራ ለመቀየር፣ አዲስ ጓደኛ ለመያዝ፣ አዲስ ንግድ ለመጀመር፣ እና የመሳሉትን ሁሉ ለማድረግና ለመቀየር በጣም እንቸገራለን፡፡ በተለይም፣ በቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ ላለን ሰዎች አዲስ የአሠራር መንገድ መቀየር በጣም Read more…

ለአገልግሎት ማብቃት

በቤተ ክርስቲያናችሁ ጌታን ማገልገል ፈልጋችሁ የሚያቀርባችሁ ሰው አጥታችሁ ታውቃላችሁ? በአንዳንድ ቤተ ክርስቲያን ዘመድ ወይም ጓደኛ ካልሆናችሁ አገልግሎት ማግኘት አትችሉም፡፡ በአንዳንድ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በዕውቀት የምትበልጧቸው ከሆነ፣ ወደ አገልግሎት በተለይም ወደ መስበክ፣ ማስተማርና መሪነት በፍጹም ልትመጡ አትችሉም፣ ምክንያቱም ቦታችን ወይም ሥልጣናችን ይወሰዳል ብለው ስለሚያስቡ አንዳንዶቻችሁን ወደ አገልግሎት በፍጹም አያስጠጓችሁም፡፡ እናንተም በተራችሁ Read more…

ሥራና አገልግሎት

ሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌልን እያገለገለ በቤተ ክርስቲያን ላይ ላለመክበድና ሸክም ላለመሆን ድንኳን እየሰፋ ይኖር እንደነበረ በሐዋርያት ሥራ 18፡1-4 ላይ እናገኛለን፡፡ ስለ ሥራ ስናስብ ኃጢአት ያመጣብን እንደ ሆነ የምናስብ ብዙዎች ነን፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስንመለከት፣ ገና ከመጀመሪያው የዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔደን ገነት አኖረው” (ዘፍ. Read more…

የለውጥ አስፈላጊነት

ሳውል ሳይወድ በግድ ወደ ጌታ መጥቶ ድነትን አገኘ፡፡ በገላትያ 1፡17-18 ላይ እንደሚናገረው፣ ወደ ዓረብ አገር 3 ዓመት ቆይቶ ከመጣ በኋላ በሐዋርያት ሥራ 9፡20 ላይ እንደምናየው ደግሞ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በምኵራቦቹ ሁሉ መስበክ ጀመረ፡፡ ወደ አገልግሎትም ሲመጣ በቁጥር 26 ላይ እንደምናነበው፣ የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን በአሳዳጅነቱ ስለምታውቀው፣ እንኳንስ አገልግሎቱን Read more…