ችግር ፈቺ

በዘመናት ስንመለከት ቤተ ክርስቲያንን በጣም የሚያሰቸግራት፣ የሚያደክማት፣ የሚከፋፍላትና የሚያጠፋት የውጭ ችግር ሳይሆን፣ የውስጥ ችግር ነው፡፡ ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 3 ጀምሮ እስከ 5 መጨረሻ ድረስ ቤተ ክርስቲያንን እያስቸገራት የመጣው የውጭ ችግር ቢሆንም፣ እያሸነፈች፣ እየሰፋችና እያደገች ሄዳለች፡፡ ከዚያ በኋላ ግን የውስጥ ችግሮች እየተፈታተኗት መምጣት ጀመሩ፡፡ የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ያላትን በማምጣት፣ በማካፈልና አብሮ Read more…

የእውነት ቃል

እግዚአብሔር አፍ የሰጣችሁ እንድትናገሩበት ሲሆን፣ ‹‹ዝም በሉ አትናገሩ›› ብትባሉ ምን ይሰማችኋል? እኔ  በደርግ ዘመን በእስር ቤት በነበርኩበት ጊዜ ለመናር የተቸገርኩበት ሁኔታ አጋጥሞኝ ነበር፡፡ (የኮሚኒስት ዘመን ስለ ነበረ፣ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋል፣ ብዙ ክርስቲያኖችም ታስረዋል፣ መጽሐፍ ቅዱስም በእጅ ይዞ መሄድ አስቸጋሪ ነበረ፡፡) ከታሰርኩበት ቀበሌ ወደ ከፍተኛው ጽሕፈት ቤት ተወስጄ፣ ከተለያየ ሥፍራ Read more…

ድንቅ ስጦታ

የሐዋርያት ሥራ 3፡1-10 ላይ ስንመለከት እንደሚነግረን አንድ ከእናቱ ማህጸን ጀምሮ አካል ጉዳተኛ የነበረ ሰው መልካም በሚሉአት ደጅ የቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ በየቀኑ የሚያስቀምጡት በሽተኛ ነበረ፡፡ እርሱም ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ መቅደስ ለጸሎት ሲገቡ አይቶ  ለመናቸው፡፡ ጴጥሮስም ትኩር ብሎ ተመልክቶት ወደ እኛ ተመልከት አለው፡፡ በሽተኛውም ምጽዋት የሚሰጡት መስሎት ወደ እነርሱ በጉጉት ዓይኑን Read more…

አስደናቂ ፈውስ

 በሥጋችሁ ላይ ባለ ሕመም ድንቅ ፈውስ ተመኝታችሁና ናፍቃችሁ ታውቃላችሁ? ይህ የሁላችንም መሻት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ታማችሁ ፈውስን ፍለጋ በየቦታው ስትባዝኑ ከርማችሁ ባለማግኘታችሁ ምን ተሰማችሁ?  ማንን ረዳት አገኛችሁ? ባለ መፈወሳችሁስ ግራ አልተጋባችሁም? አላዘናችሁም? ተስፋ አልቆረጣችሁም? ፈውስ እየፈለጉ አለመፈውስ፣ ከበሽታ ነጻ መሆን እየፈለጉ ነጻ አለመሆን፣ መዳን እየፈለጉ አለመዳን፤ ያስለቅሳል፣ ያነጫንጫል፣ ተስፋ Read more…

ፍርድ የተደባለቀበት ተስፋ

በኢሳይያስ የተነገረው ትንቢት፣ ባለመታዘዛቸው ምክንያት፣ የመጀመሪያው ፍጻሜ ያገኘው በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደ ነበረ ተመልክተናል፡፡ እንደገና በ70 ዓ.ም የአይሁድ ሕዝብ በእግዚአብሔር ፍርድ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ እንደምትወድቅ ስላወቀና ትንቢቱ እንደሚፈጸምባት ስለተረዳ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብዓዊ ሆኖ በመጣ ጊዜ ለኢየሩሳሌም ዘመድ እንደሞተበት ሰው እንዳለቀሰላት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ (ሉቃ.13፡31-35፤ 19፡41-44) አሁንም የአይሁድ ሕዝብ የሰላማቸውን Read more…

የተሰቀለው ጌታ

ጴጥሮስ ሕይወት-ለዋጭ ስብከቱን ኢየሱስን ማዕከል በማድረግ ያቀርበዋል፤  “የእሥራኤል ሰዎች ሆይ ይህን ቃል ስሙ፣ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተዓምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፡፡”… “እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን  እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእሥራኤል ወገን ሁሉ ይወቅ፤” ብሎ ዋናውን ቁም ነገር ለሕዝቡ አስጨበጠ፡፡ Read more…

አለመታዘዝ

‹‹በአንድ ድንጊያ ሁለት ወፍ››  እንደሚሉት፣ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ሁለት ሦስት ሐሳቦችን በአንድ ጊዜ መግለጽ ይችላል፡፡ ስለዚህ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሁለትን ስንመለከት የሁለት ነገሮች ፍጻሜ ነው፡፡ የመጀመሪያው ለወንጌሉ ሥራ ኃይል የሚሆን የተስፋ ፍጻሜ ሲሆን፣ ሁለተኛው ወንጌልን ባለመቀበላቸውና ባለመታዘዛቸው የሚመጣ የፍርድ ፍጻሜን ያመለክታል፡፡ በብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስና መንፈስ ቅዱስ የተነገሩ ትንቢቶች ለአይሁዶች Read more…

ሕይወት- ለዋጭ መልእክት

ምዕራፍ አንድ ታላቁ ተልዕኮ የሚለውን ጨርሰን፣ ወደ ምዕራፍ ሁለት ታላቁ ተልዕኮ በኢየሩሳሌም ወደሚለው ርዕስ መግባት ጀምረናል፡፡ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2፡14-36ን ስንመለከት ጴጥሮስ በበዓለ-ኀምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስ ከተሞላ በኋላ፣ ለበዓሉ ለተሰበሰቡት ሕዝቦች፣ ሕይወት-ለዋጭ የሆነውን ስብከት እንደ ሰበከ እናገኛለን፡፡ የሰውን ሕይወት ሊለውጥ የሚችል ስብከት መያዣና መጨበጫ የሌለው ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ ዮሐንስ ራዕይ Read more…

የተልዕኮው አድማስ

በታላቁ ተልዕኮ ውስጥ ሦስተኛው ሀሳብ “ምስክሮቼ ትሆናላችሁ”  የሚል ነው፤ መንፈስ ቅዱስን መስጠትና ኃይል መስጠት የእግዚአብሔር ድርሻ ሲሆን፣ ምስክር መሆን የሐዋርያት ድርሻ ነበር፡፡ ጌታ ተልዕኮውን ለመወጣት የተጠቀመበት ስልት ሐዋርያትን መጠቀም ነበር፤ በምድር በነበረበት ጊዜ ሦስት ዋና ዋና ነገሮች አድርጎአል፡፡ የመጀመሪያው ለአባቱ ክብር መስጠት፣ ሁለተኛው ጥቂቶችን በማሰልጠን  ጊዜ መውሰድ ሲሆን፣ ሦስተኛው ተልዕኮውን Read more…