ትንቢቱ The Prophecy

ለመሆኑ የመንፈስ ቅዱስ ተስፋ በብሉይ ኪዳን ተነግሮ ነበር? እስቲ የተወሰኑ በብሉይ ኪዳን የተነገሩ ትንቢቶችን እንመልከት፡፡ ኢዩኤል ከ800 ዓመት በፊት፣ “መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ አፈሳለሁ” (2፡28) ሲል፣ ሕዝቅኤል ደግሞ፣ “…አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ … መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ … ” (36፡26-27) በማለት እግዚአብሔር ወደፊት በልጁ በኩል መንፈስ ቅዱስን ለሚያምኑበት ሁሉ እንደሚሰጥ በትንቢታቸው Read more…

ዋናው ተልዕኮ

ሐዋርያት ትኩረታቸውን በተልዕኮ ላይ እንዳላደረጉ ባለፈው ተመልክተናል፡፡ ለመሆኑ፣ ተልዕኮ ምንድን ነው?  እስከ አሁንም ተልዕኮ፣ ተልዕኮ ስንል ብዙ ቆይተናል፤ ብዙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የተለያዩ የግል ድርጅቶች አሁን አሁን ላይ ስንመለከት ሁሉም ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች በማለት የማንነታቸው መገለጫዎችን ይጽፋሉ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረበት ጊዜ ተልዕኮ ነበረው፤ ተልዕኮውም የሰው ልጆችን ከአብ ጋር Read more…

ተልዕኮን መወጣት

ሰዎች በዚህ ዓለም ሲኖሩ በተለያየ ነገር ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ በክብር፣ በዝና፣ በገንዘብ፣ በዘር፣ በጐሣ፣ በቋንቋ እና በመሳሰሉት ነገሮች ሁሉ ላይ ትኩረት በማድረግ ጊዜያቸውን፣ ኃይላቸውንና ሕይወታቸውን ለዚያ ነገር ይሰጣሉ፡፡ በዚህ ምድር በምንኖርበት ጊዜ ትልቅ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር ተልዕኮ መሆን አለበት፡፡ ሐዋርያት ለ3 ዓመት ተኩል በጌታ በራሱ እንኳን ሰልጥነው Read more…

መንፈስ ቅዱስ

ሐዋርያት በጌታ የተሰጣቸው ትዕዛዝ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ፣ አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል እንዲጠብቁና በመንፈስ ቅዱስ እንዲጠመቁ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን ብዙ የገባቸው አልመሰለኝም፣ ይህን ያልኩበት ምክንያት የሐዋርያት ሥራ 1፡6 ላይ ከትንሣኤ በኋላ ስለ ምድራዊ መንግስት ሲጠይቁት ይታያሉ፡፡ ለነገሩ ባይገባቸውም የሚያስደንቅ አይደለም፣ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ስለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ተጽፎ የምናገኘውና ግልጽ የሆነ ነገር Read more…

አንድ ልብ

ባለፈው ተለቆ ባየነው ጽሑፍ ሐዋርያት ጌታ ካረገ በኋላ፣ በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት መሰብሰባቸውን አንብበናል፡፡ እግዚአብሔር ሥራው እንዲሠራ ከሁሉ በላይ አንድ ልብ ይፈልጋል፡፡ የሐዋርያት ሥራ 1፡14፤ 2፡1፣46፤ 4፡26፣32፤ 5፡12  በእነዚህ ሁሉ ጥቅሶች ስንመለከት በአንድ ልብ ሆነው ወደ ጌታ የቀረቡበትን ሁኔታ እናገኛለን፡፡ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ለማግኘት አንድ ልብ መሆን እንደ ጠቀማቸው እናያለን፡፡ Read more…

የተስፋውን ቃል መጠበቅ

ተስፋ የማናየው የማንጨብጠው ወደፊት የሚጠበቅና የሚፈጸም ነው፡፡ ተስፋ ባይኖር የሰው ልጅ በዚች ምድር ላይ መኖር አይችልም ነበር፡፡ የታመመ እድናለሁ፣ የከሰረ አተርፋለሁ፣ ሥራ ያጣ አገኛለሁ፣ ፈተና የወደቀ አልፋለሁ ብሎ ተስፋ ባይኖረው ኖሮ፣ የሰው ልጅ የዚህን ዓለም ችግርና ፈተና ተቋቁሞ አሁን የደረሰበት ባልረሰ ነበር፡፡ ይህ ተስፋ እግዚአብሔር  ሰውን ሲፈጥረው በውስጡ ያስቀመጠለት ስጦታው Read more…

ሕያው ጌታ

ጌታ ሞትን ድል አድርጎ ሕያው ሆኖ በመነሳት ለዐርባ ቀን ራሱን አሳያቸው፡፡ በዚህ ዐርባ ቀን ውስጥ ወደ አሥራ አንድ ጊዜ ራሱን ሲገልጥ የታየው ለአማኞች ብቻ ነበረ፡፡ ለመግደላዊት ማርያም፣ ለእነ ጴጥሮስ፣ ለኤማሆስ መንገደኞች፣ ለአሥራ አንዱና ለአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት በተለያየ ጊዜና ለሌሎችም … መታየቱን ከሚከተሉት ጥቅሶች መረዳት እንችላለን፡፡  ‹‹…ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ…››፣ Read more…

የተልዕኮው ትዕዛዝ

ሉቃስ የጳውሎስን ታሪክ በስፋት የጻፈው ለምንድነው? የሚለውን ቀደም ብለን ጠይቀን ነበር፡፡ ሉቃስ ስለ አህዛብ መለወጥ ከመጻፉ በፊት ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠውን ተስፋውን የመጠበቅ ትዕዛዙን እንደ መግቢያ ተጠቅሞበታል፡፡ የመልእክቱ የመጀመሪያ ዓላማ  ሕያው የሆነው ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላ በመቀጠል ያደረገውንና የሠራውን ለወዳጁ መግለጽ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ፣ ጸሐፊው ትልቅ ትኩረት የሰጠው ስለ አሕዛብ Read more…